Testimonials
I had an excellent experience at MeQrez. The staff was compassionate and attentive, and the facilities were clean and well-maintained. The doctors and nurses provided top-notch care, explaining everything thoroughly and ensuring my comfort throughout my stay. Dr. Miskir, Sister Kidist & Dr. Kibrom, thank you so much for your exceptional care. Highly recommended!
I am proud to be a shareholder of MeQrez. I've experienced their services firsthand and found them to be both efficient and compassionate. The nurses and doctors treat you like family, and all at a reasonable price.
Simply The Best Hospital in the country. The way of their hospitality is just on another level, the physicians are great professionals and Wise. Happy to be there. Finally i want to say tnx for all of you guys at MeQrez
የዚህ ዓይነት ሆስፒታሎች
_#መቅረዝ ሆስፒታል #ጋዜጠኛ ምስጋናው ታደሰ ሰሞኑን የተኛበት ነው። አንድ የታዘብኩትን ነገር መናገሩ አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘሁት ነው። ወደዛ እንዴት ሄደ የሚለውን የአካሄድ ዝርዝሩን ለጊዜው ልለፈው እና ልቀጥል
የግል ሆስፒታሎች በብዛት ያላቸው ዋጋ ይታወቃል እንደግልጋሎት እንደደረጃው ሂሳባቸውም ይወሰናል ብዬ አምናለሁ። የህክምና ተቋማት ከስማቸው ይልቅ ዋጋቸው ከግልጋሎታቸው አንፃር ቢገመገም እመርጣለሁ። የነርሶቹ ትህትና እና ትዕግስት ከጥበቃ ጀምሮ ያለው ስነስርዓት መልካም ነው ( ስለገንዘብም ነው ቢባል እንኳን ያም ሆኖ ብዙ የፀባይ ደሃ አለ) የጥበቃ ሰዎችም ጠያቂን መከልከል እና መፍቀዳቸው አይደለም ትልቁ ነጥብ እሱ ስራቸውም ነው እነሱንም መረዳት ተገቢ ነው። ትልቁ ነገር ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚግባቡበት መንገድ ነው ወሳኙ ብዬ አምናለሁ(ኮሚዩኒኬሽን ትልቁ ነጥብ) ግላዊ ክብር ሳይነካኩ ሳይጎራበጡ ማስረዳትም ይቻላል።
#ዋናው ነጥቤ
ምስጋናው አገባቡ በድንገተኛ ነበር እናም የመጀመሪያ ህክምና እርዳታን እስኪሰጡ ድረስ ስለብርም ሆነ ስለካርድ እያወሩ አልነበረም።እንደውም ቆይተው የሌላውንም ሰው መረጋጋትን ካዩ በኋላ ነበር ወደቀጣዩ የሄዱት። እርግጥ ይሄ መደበኛ ነገር ነበር ሆኖም ስናጣው የሚከፋንን ያህል መኖሩንም ማጉላት ያስፈልጋል። ቀጥሉበት፣ አዎ ቅደም ተከተሉን በደንብ መጠበቁን ግፉበት ለማለቱም ነው🙏
#ሰውክቡር_ክቡርሰው!
ባጋጠመኝ መጠነኛ ሕመም ሆስፒታሉ የሰጠኝን አስገራሚ አገልግሎት ምስክር መኾን እንደሚገባኝ አምኜበታለሁ።
ከሁሉም የገረመኝ ወደ ሆስፒታሉ ገና ከመድረሴ አስቸኳይ የሕክምና አገልግሎት ሰጥተው እስኪጨርሱ ድረስ ቀድሜ ካርድ እንዳወጣ ሳያስገድዱኝ ጤንነቴ መለስ ብሎ እፎይታ እስካገኝ እነሱ ትኩረታቸው ጤናዬ ላይ ብቻ ነበር።
ይህ ነገር ለኔ ብቻ የገጠመኝ እንደሆነ ለማወቅ ሌሎችን ሰዎች ስጠይቅ ለሁሉም ሰው የሚያደርጉት ቋሚ አሰራራቸው መኾኑን ሰማሁ። የገጠሙኝ ሀኪሞች ብቃት ትህትና እና የቤቱ ንጽሕና የሆስፒታል ፎቢያዬን ገፎልኛል ብል እያጋነንኩ አይደለም።
ከታች ያያያዝኩትን ማስታወቂያ እንዳየሁት ያለማንም ጠያቂነት በገዛ ፍቃዴ ለስራቸው እውቅና ለመስጠት ስል ከዚህ ምስክርነቴ ጋር ወድጄ ያለምንም ክፍያ አጋርቼያችኋለሁ።
MeQrez Health Services S.C በርቱ
ከፈጣሪ በታች የተቸራችሁን የህክምና ጥበብ ተጠቅማችሁ ህይወቴን ስላተረፋችሁ እና ስለ መልካም አቀባበላችሁ እንክብካቤያችሁ አመሰግናለሁ።የአገልግሎት ዘመናችሁ ይባረክ ከታላቅ አክብሮት ጋር
Previous
Next