Search

Blog

ብጉር ( Acne vulgaris)

April 30, 2024

ብጉር ( Acne vulgaris)

ብጉር ወዝ አመንጪ እጢዎች ተከማችተው በሚገኙባቸው የአካል ክፍሎች ላይ (ፊት ፣ ደረት ፣ የላይኛው የጀርባ ክፍል) የሚወጣ የቆዳ ህመም አይነት ነው።
በሁሉም የዕድሜ ክልል የሚከሰት ሲሆን  በአብዛኛው ከ12-25 የእድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ወጣቶች ላይ ይታያል።
ብጉር አብዛኛውን ጊዜ ወንዶች ላይ የሚከሰት ሲሆን ከወጣትነት የእድሜ ክልል በኋላ (30 እና 40ዎቹ) የሚከሰተው የብጉር አይነት ግን በብዛት ሴቶች ላይ ይታያል።
ለብጉር መከሰት መሰረታዊ ሁኔታዎች
1-የሞቱ የቆዳ  ህዋሳት ተጠራቅመው የወዝ መተላለፊያ ቱቦ ሲዘጋ
2-የወዝ ምርት መጨመር
3-ዘወተር ቆዳ ላይ የሚገኘው ነገር ግን የወዝ መባዝትን ተከትሎ  የሚያድገው ፕሮፒዩኒባክቴሪየም አክኒ የተባለው ባክቴሪያ መብዛት
4-ይህን ተከትሎ የሚመጣው ብግነት

ለብጉር መከሰት ምክንያቶችና አባባሽ ነገሮች

1.የሆርሞን ለውጦች
በጉርምስና ጊዜ የሚኖር የሆርሞን ለውጦች የወዝ እምራች እጢዎችን እንዲተልቁና የወዝ ምርት እንዲጨምር ያደርጋሉ
በወር አበባ ሰሞን ሊባባስ ይችላል
አንዳንድ ጊዜ ሴቶች ላይ የአንድሮጅን ሆርሞን መብዛት ለብጉር  ምክንያት ሊሆን ይችላል
2. ውጫዊ ምክንያቶች
-ብዙ ጊዜ ብጉር ያለባቸው ሰዎች የተለያዩ ሳሙናዎችንና ምርቶችን  ሲጠቀሙ ይታያሉ ፣ሳሙናዎቹ ቆዳ ላይ ያለውን ወዝ  ሲቀንሱ ነገር ግን የወዝን ምርት የመቀነስ አቅም የላቸውም ።በተደጋጋሚ በነዚህ ሳሙናዎችና ምርቶች ማሸትና መቀባት ብጉሩ እንዲፋቅና ለኢንፍላሜሽን እንዲጋለጥ ያደርገዋል ይህም ብጉሩ እንዲባባስ ሊያደርገው ይችላል።ስለዚህ ብጉር ያለባቸው ሰዎች ፊታቸውን በሃይል ማሸት የለባቸውም።
-በቆዳችን ላይ በሚከሰተ መፈጋፈግ ወይም ጫና  ለምሳሌ በህመም ሆነ በሌላ ምክንያት ለረጅም ግዜ በጀርባው የሚተኛ ሰው ጀርባው ላይ ብጉር ሊወጣ ይችላል ወይም የጡት ማስያዣ ገመድ የሚያርፍባቸው ቦታዎች ላይ ሊወጣ ይችላል
3 የቤተሰብ ሁኔታ(Family History)
ብጉር ያለበት የቤተሰብ አባል ሲኖር(ወንድም፣እህት፣እናት፣አባት) መኖር ከሌላው ሰው የተለየ ተጋላጭነትን ይጨምራል
4.ጭንቀት (stress),ከመጠን ያለፈ ውፍረት ተጠቃሽ ናቸው።

ብጉር ለምን ይታከማል?

-ብጉር ከሚያሳድረው የስነ-ልቦና ጫና በተጨማሪ ሳይታከም በቆየ ቁጥር ፊታችን ላይ ጠባሳ የመፍጠር እድሉ የሰፋ ስለሆነ በጊዜ መታከሙ ይመከራል።
ብጉር እንዴት ይታከማል
-የብጉር ህክምና እንደ ብጉሩ አይነትና ደረጃ መጠን በሚቀባ ፣ በሚቀባና በሚዋጥ ወይም በሚዋጥ መድሀኒት ሊታከም ይችላል
– እንዳስፈላጊነቱ የተለያዩ  ለብጉር ህክምና  የተሰሩ ሳሙናዎችንና መታጠቢያዎችን መጠቅም ሊኖርብን ይችላል
ብጉር ያለበት ሰው እነዚህን ነገሮች ማድረግ ይኖርበታል
-እንቅስቃሴ ማድረግ
-ጠባሳ እንዳይፈጠር  ብጉሮቹን ለማፍረጥ አለመሞከር
-Oil-free & non-comedogenic  የሆኑ የውበትና የቆዳ ጤና መጠበቂያ ምርቶች መጠቀም
-በሀኪም የታዘዙ ፀሐይ መከላከያ (sun-screen) መጠቀም
-ቆዳችን ላይ ጫና የሚፈጥሩ ነገሮችን (የፊት ማስክ፣ሄልሜት ,፣ስልክ፣ የቦርሳ/የጡት ማስያዣ ገመድ) መቀነስ
ብጉርና እርግዝና
ለማርገዝ ያቀዱ እንስቶች ከማርገዛቸው በፊት የብጉር መድሃኒቶችን ለማቆም ማሰብ ይኖርባቸዋል ሆኖም  ህክምናው አስፈላጊ ከሆነ ኃኪማቸውን ማማከር ይገባል።

መቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል ቢመጡ የአመታት ልምድ ያካበቱ የቆዳ ህክምና ስፔሻሊስት ኃኪሞችን  ያገኛሉ።

ዶ/ር ሊሻን ደመረ የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት ሃኪም ሲሆኑ ረቡዕ ከ08:00- 11:00 እንዲሁም አርብ ከ 4:00-06:00 ይገኛሉ።
ዶ/ር ህይወት እንግዳወርቅ የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት ሃኪም ሲሆኑ   ቅዳሜ ከ 02:00-06:00 ይገኛሉ።
ዶ/ር ሰሎሞን ወርቁ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት ሲሆኑ ሐሙስ ከ 10:00-12:00 ይገኛሉ።
ዶ/ር ህሊና ተኮላ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት ሲሆኑ ሰኞ ከ 03:30-06:00 ሰዓት እንዲሁም ማክሰኞ ከ 07:00-11:00 ይገኛሉ።

ቀጠሮ ለማስያዝ 0952272727 ወይም 6757 ላይ ይደውሉ።