ለአጥንት ጥንካሬ የሚረዱ የምግብ አይነቶች
በዶ/ር ሀብተወልድ ሙላት
****
ለሰውነታችን ጥንካሬ እና ጤንነት የአጥንታችን ጤንነት ወሳኝ ነው።
ለዚህም ደግሞ አጥንታችንን ለማጠንከር የሚረዱን የተለያዩ የምግብ አይነቶች አሉ ። እነዚህም
1. አትክልት፦ አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው እና ለምግብነት የምንጠቀማቸው አትክልቶች በሚኒራል ንጥረ ነገር የበለጸጉ ስለሆኑ ለአጥንታችን ጤንነት እና ጥንካሬ እጅጉን ጠቃሚ ናችው ከሚባሉ የምግብ አይነቶች ይመደባሉ።ምክንያቱም እነዚህ ለምግብነት የሚውሉ አትክልቶች ለአጥንት ጤንነት ጠቃሚ የሆኑ እንደማግኒዚየም፣ ፎስፈረስ፣ ፖታሲየም እና አይረን መገኛ በመሆናቸው ለአጥንታችን ጥንካሬ ጠቃሚ ናችው።
2. በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦች፦ እንደ ወተት፣ አንቁላል፣ አሳ፣ የአኩሪ አተር ወተት፣ ኦቾሎኒ የመሳሰሉ ምግቦች በፕሮቲን የበለጸጉ የምግብ አይነቶች ሲሆኑ ለአጥንታችን ጤንነት እጅጉን ጠቃሚ በመሆናቸው እነዚህን አዘውትረን በአግባቡ መጠቀም ለአጥንታቸን ጥንካሬ ከፍ ተኛ የሆነ ጠቀሜታ አለዉ።
3. ጥራጥሬዎች፦ ለምግብነት የሚውሉ ጥራጥሬዎች የካርቦሀይድሬት ንጥረ ነገር መገኛ በመሆናቸው ለአጥንት ጥንካሬ ብንመገባቸው ተብለው ከሚመደቡ የምግብ አይነቶች ናቸው።
እንደ አጃ፣ ሩዝ፣ በቆሎ ያሉ የጥራጥሬ እህሎች ዱቄቶች ውስጥ ካርቦሀይድሬትን በቀላሉ ስለምናገኝ በተለያዩ አይነት አዘገጃጀቶች በምግባችን ውስጥ አስገብተን መጠቀምም አጥንታቸንን ለማጠንከር የራሳቸው የሆነ ጠቀሜታ አላቸዉ።
ዶ/ር ሃብተወልድ ሙላት የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሃኪም ሲሆኑ ሰኞና አርብ ከ 07:00-11:00 ይገኛሉ።