Cataract (የሞራ ግርዶሽ)
Cataract (የሞራ ግርዶሽ) ሌንስ ጥራቱን በተለያዩ ምክንያት ሲያጣ – በተለያየ መጠን ወደ ነጭነት ሲቀየር እና ዋናዉ አገልግሎቱ ሲታወክ – ሞራ ግርዶሽ ተከሰተ ይባላል፡፡
• ሌንስ የምንለው የዓይን ፊተኛዉ ክፍል ዉስጥ ያለ ንዑስ-ዓይን አካል ሲሆን በተፈጥሮዉ ጥርት ያለ ነዉ፡፡ ስራዉ ብርሃንን ወደ ኃለኛዉ የዓይን ክፍል የብርሃን ግድግዳ (ሬቲና) መርቶ ማሰተላለፍ አንዱ ነዉ፡፡
• የሞራ ግርዶሽ ዓይነ-ስውርነትን ከሚያመጡ ምክንያቶች በዓለም ላይ በአንደኛ ደረጃ ይቀመጣል ፡ ይህም ከግማሽ በላይ ይይዛል፡፡
ምክንያቶች
ሞራ ግርዶሽ አብዛኛዉ ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ሲሆን ሌሎች ምክንያቶች ስኳር ፣ከግርዶሹ ጋር አብሮ በመወለድ፣ በአደጋ ፣ በስቴሮይድ መድሃኒት ከመጠቀም ጋር የተየያዘ፣ አልትራቫዮሌት ጨረር፣በዉስጣዊ የዓይን ቁጣ፣… ወዘተ የመሳሰሉት ሊከሰት ይችላል።
ምልክቶች
• የደበዘዘ ወይም ደመናማ እይታ
• በምሽት የማየት ችግር
• ብርሃን መፍራት
• በብርሃን ዙሪያ ሃሎዎችን ማየት
• በሐኪም የታዘዙ መነጽሮች ላይ ተደጋጋሚ ለውጦች
• ከለሮች ስናይወደ ቢጫ መቅለም
• ድርብ እይታ
መከላከያ መንገዶች
• የዓይን ሞራ ግርዶሹን ቶሎ ለመለየት በየጊዜው የዓይን ምርመራዎች ማድረግ
• እንደ የስኳር በሽታ ያሉ የጤና ችግሮችን መቆጣጠር
• ዓይንን ከአልትራቫዮሌት ጨረር ለመከላከል የፀሐይ መነፅር ማድረግ
• ማጨስን እና ከመጠን በላይ አልኮል ከመጠጣት መቆጠብ
• በፀረ-ኦክሲዳንት የበለፀገ ጤናማ አመጋገብን መጠበቅ የአይን ጤናን ይደግፋል
ህክምናው
• የሞራ ግርዶሽ በቀዶ ህክምና አማካኝነት ይታከማል።
መቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል ቢመጡ የአመታት ልምድ ባካበቱ የአይን ስፔሻሊስት ሃኪሞች ከፍተኛ ጥራት ያለው የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ያገኛሉ።
ሰኞና ማክሰኞና ቅዳሜ ከ 02:00-06:00 ዶ/ር በእምነት ፈለቀ
ረቡዕ ከ 09:00-11:00 ዶ/ር አለማየሁ ወልደየስ
ሀሙስ ከ 08:00-11:00 ዶ/ር ሳራ አበባው
6757/0921636465/0952272727 ይደውሉ