Search

Blog

ማር

June 24, 2024

                       ማር(Honey)

• ማር የአበባ አብቃይ የሆኑ እፅዋትን በመጠቀም በማር ንብ የሚሠራ ጣፋጭ ፈሳሽ ነው። ወደ 320 የሚጠጉ የተለያዩ የማር ዝርያዎች አሉ።እነሱም በቀለም፣ ጠረን እና ጣዕም ይለያያሉ።

• ማር በአብዛኛው ስኳር እንዲሁም አሚኖ አሲዶች ቫይታሚኖች ማዕድናት ብረት ዚንክ እና አንቲኦክሲደንትስ ድብልቅን ይዟል። ማር እንደ ተፈጥሯዊ ጣፋጭነት ከመጠቀም በተጨማሪ እንደ ፀረ-ብግነት፣እና ፀረ-ባክቴሪያሆኖ ያገለግላል።ሰዎች ብዙ ጊዜ ቁስሎችንና ሳልን ለማከም ለማከም ማርን ሲጠቀሙት ይታያል።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት
ለተወሰኑ ሁኔታዎች በማር ላይ የተደርጉ ምርምሮች የሚከተሉትን ያጠቃልላል ።

  • የልብና አየደም ስር በሽታን ይቀንሳሉ :- በማር ውስጥ ያሉ አንቲኦክሲደንትስ የልብ በሽታ ተጋላጭነትን መቀነስ ጋር ተያይዞ ሊሆን ይችላል።
  • ለሳል ማስታገሻነት ያገለግላል:- ጥናቶች እንደሚያሳዩት የባሕር ዛፍ ማር፣ ሲትረስ ማር እና አንዳንድ የማር አይነቶች ለአንዳንድ የላይኛው የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን እና አጣዳፊ የሌሊት ሳል ላለባቸው ሰዎች እንደ ሳል ማስታገሻ መድኃኒትነት ሊያገለግሉ ይችላሉ።
  • ለአንጀት መቆጣት በሸታ :-መረጃዎች እንደሚያሳዩት ማር ከአንጀት መቆጣት በሽታ ጋር ተያይዞ እንደ ተቅማጥ ያሉ የአንጀት ህመሞችን ለማስታገስ ይረዳል።
  • ለነርቭ በሽታ :- ጥናቶች እንደሚያሳዩት ማር ለጭንቀት ፣ ለሚጣጥል በሸታ እና ለድብርት ህመሞች ጥቅሞችን ይሰጣል። በአንዳንድ ጥናቶች ማር የማስታወስ ችግርን ለመከላከል እንደሚረዳ ተመላክቷል።

ቶሎ ቁስል እንዲድን ይረዳል:- ማርን በመቀባት ጥቅም ላይ ማዋል ቁስሎችን መፈወስን እንደሚያበረታታ ታይቷል፣በተለይም በቃጠሎ የሚመጡ ቁሰሎች ቶሎ እንዲድኑ አስተዋፅኦ ያደርጋል።
ውጤቶቹ ሊለያዩ ይችላሉ ምክንያቱም ማር ለማምረት ወይም ጥራቱን ለማረጋገጥ ደረጃቸውን የጠበቁ ዘዴዎች የሉም።(no standardized methods)

ማር በአጠቃላይ በአዋቂዎች እና ከ 1 አመት በላይ ለሆኑ ህጻናት ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።

ደህንነት እና የጎንዮሽ ጉዳቶች

ማር ለቀላል ቁስሎች እና ቁስሎች እንደ ተፈጥሯዊ ማጣፈጫ፣ እንደ ሳል ማስታገሻ ለመጠቀም ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።

ከ 1 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት ማር – ትንሽ ጣዕም እንኳን ቢሆን ከመስጠት ይቆጠቡ! ማር ለክሎስትሪዲየም ቦቱሊነም ስፖሮች በመጋለጥ የሚከሰት ያልተለመደ ነገር ግን ከባድ የሆድ ህመም (የጨቅላ ቦትሊዝም) ሊያስከትል ይችላል። ከስፖፕርሱ የሚመጡ ተህዋሲያን በህጻን አንጀት ውስጥ በማደግ እና በመባዛት አደገኛ መርዝ ያመነጫሉ።

አንዳንድ ሰዎች በማር ውስጥ ለተወሰኑ ክፍሎች በተለይም የንብ ብናኞች ስሜታዊ ወይም አለርጂዎች ናቸው። ምንም እንኳን ያልተለመደ ቢሆንም የንብ ብናኝ አለርጂዎች ከባድ እና አንዳንድ ጊዜ ገዳይ ምላሽ ሊያስከትሉ ይችላሉ።ማርን ከተጠቀሙ በኋላ አለርጂክ ከሆኑ የሚኖሩ የምላሽ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:

• የአስም ምልክቶች
• መፍዘዝ
• ማቅለሽለሽ
• ማስታወክ
• ድክመት
• ከመጠን በላይ ላብ
• ራስን መሳት
• መደበኛ ያልሆነ የልብ ምት (arrhythmias)
• ማሩን ከተቀቡ በኋላ የተቀቡበት ቦታ ላይ ውጋት መኖር

#health_tips
#honey

References
1. Armstrong DG, et al. Basic principles of wound management. https://www.uptodate.com/contents/search. Accessed june 23, 2024.
2. Meo SA, et al. Role of honey in modern medicine. Saudi Journal of Biological Sciences. 2017;24:975.
3. Samarghandian S, et al. Honey and health: A review of recent clinical research. Pharmacognosy Research. 2017;9:121.
4. Honey. Micromedex 2.0 Healthcare Series. http://www.micromedexsolutions.com. Accessed june 23, 2024.

መቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል
6757/0952272727/0921636465