Search

Blog

ለምፅ / ቪቲሊጎ

June 25, 2024

የዚህ ጽሁፍ አላም በለምፅ ዙሪያ አምስት የተለመዱ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ማስወገድ ነው።

 

ስለ ለምፅ 5 የተለመዱ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ማስወገድ

#የተሳሳተ_አመለካከት 1:

ለምፅ ተላላፊ ነው።

 

እውነታ፡

 

ለምፅ ተላላፊ አይደለም እና ከተጎዳው ሰው ጋር በመገናኘት ሊተላለፍ አይችልም.።በጄኔቲክ፣ በራስ-ሰር እና በአካባቢያዊ ሁኔታዎች ምክንያት የሚመጣ ተላላፊ ያልሆነ የቆዳ በሽታ ነው።

 

#የተሳሳተ_አመለካከት 2፡-

ለምፅ የሚከሰተው በደካማ ንጽህና ወይም የአኗኗር ዘይቤ ምርጫዎች ነው።

 

እውነታ፡

 

ለምፅ የሚከሰተው በንጽህና ጉድለት፣ በአመጋገብ ሁኔታዎች ወይም በአኗኗር ዘይቤዎች ምክንያት አይደለም። የ ለምፅ ትክክለኛ መንስኤ ሙሉ በሙሉ ባይታወቅም የጄኔቲክ ቅድመ-ዝንባሌ እና ራስን በራስ የሚከላከሉ ምክንያቶችን ያካትታል ተብሎ ይታመናል።

 

#የተሳሳተ_አመለካከት 3:-

ለምፅ በቆዳ ላይ ብቻ ተጽዕኖ ያሳድራል

 

እውነታ፡

 

ለምፅ በዋነኝነት ቆዳን የሚጎዳ ቢሆንም ፀጉርን፣ አይን እና የ ሙከስ ሽፋንን ጨምሮ ሌሎች የሰውነት ክፍሎችን ሊያካትት ይችላል። በአንዳንድ ሁኔታዎች ለምፅ ያለባቸው ግለሰቦች በፀጉር ቀለም ላይ ለውጥ ወይም በአይን ውስጥ ቀለም መጥፋት ሊያጋጥማቸው ይችላል።

 

#የተሳሳተ_አመለካከት 4፡-

ለምፅ ሊታከም የማይችል ነው

 

እውነታ፡

 

በአሁኑ ጊዜ ለ ለምፅ ምንም አይነት መድሃኒት ፈዋሽ ባይኖርም ሁኔታውን ለመቆጣጠር እና የተጎዳውን የቆዳ ገጽታ ለማሻሻል የሚረዱ የሕክምና አማራጮች አሉ። እነዚህ የሚቀቡ መድሃኒቶች የፎቶ ቴራፒ እና የቀዶ ጥገና ጣልቃገብነቶችን ሊያካትቱ ይችላሉ።

 

#የተሳሳተ_አመለካከት 5፡-

ለምፅ ያለባቸው ሰዎች ሌላ የጤና ሁኔታ አላቸው

 

እውነታ፡

 

አንዳንድ የ ለምፅ ያለባቸው ሰዎች እንደ ታይሮይድ እክሎች ወይም የስኳር በሽታ ያሉ ሌሎች ራስን የመከላከል ሁኔታዎች (Auto immune conditions) ሊኖራቸው ቢችልም ለምፅ ያለባቸው ሁሉ ተጨማሪ የጤና ችግሮች አላቸው ማለት አይደለም። ለምፅ በራሱ ወይም ከሌሎች ራስን የመከላከል ሁኔታዎች ጋር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል።

ለምጽ ምንድን ነው ?

ለምፅ የቆዳ ቀለም እንዲጠፋ የሚያደርግ በሽታ ነው ፡፡ በመደበኛነት የፀጉር እና የቆዳ ቀለም የሚወሰነው በሜላኒን ነው ፡፡ ቪታሊጎ የሚከሰተው ሜላኒን የሚያመነጩ ሴሎች ሲሞቱ ወይም ሥራቸውን ሲያቆሙ ነው። ቀለም የቀየሩት አካባቢዎች ብዙውን ጊዜ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ ይሄዳሉ ፡፡ ሁኔታው በማንኛውም የሰውነት አካል ላይ ቆዳን ሊያጠቃ ይችላል ፡፡ በተጨማሪም በፀጉር እና በአፍ ውስጥ ሊታይ ይችላል:፡፡ ቪቲሊጎ ሁሉንም የቆዳ አይነቶች ሰዎችን ይነካል ፣ ግን ጥቁር ቆዳ ባላቸው ሰዎች ላይ የበለጠ ሊታወቅ ይችላል ፡፡

 

ምልክቶች

 

የቪቲሊጎ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ ብዙውን ጊዜ በመጀመሪያ በእጅ ፣ በፊትዎ እና በአካል ክፍተቶች እና  ብልት አከባቢዎች ላይ ይታያል።

 

የራስ ፀጉር ፣  ቅንድብዎ ወይም ጺማዎ ላይ ያለጊዜው መነጣት ወይም ሽበት መታየት። ቪቲሊጎ በማንኛውም ዕድሜ ሊጀምር ቢችልም ብዙውን ጊዜ ከ 30 ዓመት በፊት ይታያል ፡፡ በሽታዎ እንዴት እንደሚስፋፋ ለመተንበይ አስቸጋሪ ነው  ፡፡ በአብዛኛዎቹ ተጠቂዎች የቀለም መጥፋቱ ይሰራጫል እና በመጨረሻም አብዛኛውን የቆዳዎን ክፍል ያጠቃልላል ፡፡ አልፎ አልፎ ቆዳው ቀለሙን ይመልሳል ፡፡

 

ሕክምናው

 

ሕክምና የሕክምናው ምርጫ በእድሜዎ ፣ ቆዳው ላይ ምን ያህል እንደተስፋፋ፣  ቦታው ፣ በሽታው በምን ያህል በፍጥነት እየገሰገሰ እንደሆነ እና በህይወትዎ ላይ ምን ተጽዕኖ እያሳደረ እንደሆነ ይወሰናል ፡፡ ውጤቶቹ ቢለያዩም እና ሊተነበዩ የማይችሉ ቢሆኑም መድኃኒቶችን እና ብርሃንን መሠረት ያደረጉ ሕክምናዎች (phototherapy)  የቆዳ ቀለምን ምርት ለማገዝ ይረዳሉ ፡፡ አንዳንዶቹ ህክምናዎች ከባድ የጎንዮሽ ጉዳቶች አሏቸው ፡፡ ስለዚህ  መዋቢያ (ሜካፕ) በመጠቀም  የቆዳዎትን ለምፅ ለመሸፈን እንዲሞክሩ ዶክተርዎ ሊጠቁሙዎት ይችላሉ ፡፡

 

የመድሀኒት ህክምናው ሂደት ውጤታማነቱን ለመመርመር ብዙ ወራትን ሊወስድ ይችላል። እና ለእርስዎ በጣም ተስማሚ የሆነውን ህክምና ከማግኘትዎ በፊት ከአንድ በላይ አካሄዶችን ወይም የአቀራረብ ጥምረት መሞከር ሊኖርብዎ ይችላል ፡፡ ምንም እንኳን ህክምናው ለተወሰነ ጊዜ ስኬታማ ቢሆንም ውጤቱ ላይቆይ ይችላል ፡፡

 

ቀዶ ጥገና

 

ሌሎች ህክምናዎች የቆዳ ቀለምን መመለስ ካልቻሉ ቀዶ ጥገና አማራጭ ሊሆን ይችላል. ለምፅ ለማከም ሁለት ዓይነት ቀዶ ጥገናዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ.

 

የቆዳ ንቅለ ተከላ (skin graft) : የቆዳ ህክምና ሀኪም ጤናማ ቀለም ያለውን ቆዳ አውጥቶ ወደ ለምፅ የተጠቃን የ ቆዳ ክፍል መትከል ነው።

 

የሕዋስ ንቅለ ተከላ (melanocyte transplant)፡- በዚህ አይነት ቀዶ ጥገና ወቅት ፣ የቆዳ ህክምና ሐኪም ጤናማ የሆነ ቀለም ያለው ቆዳ ይወስዳል  ከዛም የ ቀለም ሴሎችን ይወስዳል. እነዚህ ሴሎች ወደ ለምፅ የተጠቃ ቆዳ ውስጥ ይቀመጣሉ።

 

ቀዶ ጥገና ባለበት ለቆመ እና ለማይስፋፋ የለምፅ አይነት (stable vitiligo) የሚሆን የህክምና አማራጭ ነዉ።

 

የአኗኗር ዘይቤ

 

የሚከተሉት የራስ-እንክብካቤ ስልቶች ቆዳዎን ለመንከባከብ እና መልክዎን ለማሻሻል ሊረዱዎት ይችላሉ።

  • ቆዳዎን ከፀሀይ ብርሃን ይከላከሉ ፡፡ የፀሐይ መከላከያ ክሬም (sunscreen)ይጠቀሙ። እንዲሁም ጥላን መጠቀም እና ቆዳዎን ከፀሀይ የሚከላከል ልብስ መልበስ ይችላሉ ፡፡
  • ከቆዳዎ ገፅታጋ የሚመሳሰል መዋቢያዎችን (makeup ) መጠቀም።

 

አመጋገብ

  • ብዙ ውሃ መጠጣት የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓትን ያሻሽላል ፡፡
  • አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶችን ፣ ፍራፍሬዎችን እንደ ሙዝ ፣ አፕል ፣ ሽምብራ ፣ ራዲሽ እና ካሮት ያሉ  አትክልቶችን መጠቀም ጠቃሚ ነው ፡፡
  • የበሽታውን መስፋፋት ለመከላከል አልኮልን ፣ ቡና ፣ ዓሳ እና ቀይ ሥጋን ከመጠቀም ይቆጠቡ ወይም ይገድቡ ፡፡
  • ቫይታሚን ቢ ፣ ሲ ፣ አሚኖ አሲዶች እና ፎሊክ አሲዶች ያሉበት ምግብ መመገብ እነዚህን ነጭ ሽፋኖች ሊያቆማቸው ይችላል ፡፡

ማጠቃለያ

የዓለም የለምፅ ቀን 2024 ብዝሃነትን ማክበርን፣ ተቀባይነትን ማሳደግ እና ለምፅ  ዙሪያ ያሉ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ማስወገድ  አስፈላጊነትን ለማስታወስ ያገለግላል። ግንዛቤን በማሳደግ፣ ለድጋፍ በማድረግ እና ምርምርን በማጎልበት፣ ለምፅ ያለባቸው ግለሰቦች ተቀባይነት የሚያገኙበት እና በማንነታቸው የሚገመገሙበት የበለጠ ሁሉን አቀፍ የሆነ ማህበረሰብ ለመፍጠር መስራት እንችላለን።

መቅረዝ_ጠቅላላ_ሆስፒታል

መቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል ቢመጡ የአመታት ልምድ ያካበቱ የቆዳ ህክምና ስፔሻሊስት ኃኪሞችን  ያገኛሉ።

ዶ/ር ሊሻን ደመረ የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት ሃኪም ሲሆኑ ረቡዕ ከ08:00- 11:00 እንዲሁም አርብ ከ 4:00-06:00 ይገኛሉ።
ዶ/ር ህይወት እንግዳወርቅ የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት ሃኪም ሲሆኑ   ቅዳሜ ከ 02:00-06:00 ይገኛሉ።
ዶ/ር ሰሎሞን ወርቁ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት ሲሆኑ ሐሙስ ከ 10:00-12:00 ይገኛሉ።
ዶ/ር ህሊና ተኮላ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት ሲሆኑ ሰኞ ከ 03:30-06:00 ሰዓት እንዲሁም ማክሰኞ ከ 07:00-11:00 ይገኛሉ።
ቀጠሮ ለማስያዝ 0921636465  ፣0952272727 ወይም 6757 ላይ ይደውሉ።

#0952272727

#6757

#0921636465